“Lela Ewnet Yelegnem” Book Launch with Meron Getnet

📢 ቶሮንቶ ዝግጁ ናችሁ?! 🇨🇦 የተወደደችው ተዋናይት፣ ጋዜጠኛ እና ገጣሚ ሜሮን ጌትነት ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ያሰናዳቻቸውን ከ80 በላይ ጥልቅ ግጥሞች የያዘውን አዲሱንና የመጀመሪያውን የግጥም መድበል "ሌላ እውነት የለኝም!" ይዛላችሁ ልትመጣ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተዋል! በግላዊ ገጠመኞች፣ በነፍስያ እውነቶች እና ማህበራዊ ሁነቶች ላይ የሚያጠነጥኑትን እነዚህን ውብ ስራዎች አብረን ለመቋደስና ልዩ የጥበብ ከሰዓት ለማሳለፍ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። 📅 ቀን: Sunday, August 16 ⏰ ሰዓት:  3:00 PM 📍 ቦታ: 71 Gough Avenue, Toronto, ON የኪነ-ጥበብ ወዳጆች፣ የሀገር ፍቅር ስሜትና የቃላት ማዕበል የሚመስጠንን ይህንን ድንቅ የምረቃና የውይይት መድረክ እንዳያመልጥዎ! በቦታው ተገኝተን ለከያኒዋ ያለንን አክብሮትና ድጋፍ የምንገልጽበት ልዩ አጋጣሚ ነው። ቶሮንቶና አካባቢው ያላችሁ ጥበብ ወዳጆች በሙሉ ኑ፣ እንገናኝ፣ በጋራ ግሩም ጊዜ እናሳልፍ!
Read more about “Lela Ewnet Yelegnem” Book Launch with Meron Getnet
  • 0